top of page

የደብረ ገነት  መድኃኔዓለም  የመረዳጃ  ማኅበር  አጭር  ታሪክ

 

 

የደብረ ገነት መድኃኔዓለም የእድር መረዳጃ ማኅበር እንዲመሰረት ሃሳቡን በቅድሚያ ያቀረቡት ሶስት  የቤተ ክርስቲያን አዛውንት (ሀ)ሻለቃ ኃይለማርያም አባይ (ለ)አቶ ንጋቱ ጥላሁንና (ሐ)ኢንጂኔር ግርማ አላሮ ናቸው። ማሕበሩ በአባላት ፀድቆ በሕግ የተቋቋመው ግን በ2004 (1996 E.C.) ነው። 

 

የድርጅቱ ዋና ዓላማ፤ የደብረ ገነት መድኃኔ ዓለም የመረዳጃ ማኅበር ቤተሰቦችን በሀዘንና በሕመም ጊዜ እርስ በርስ ለማፅናናትና ለመረዳዳት እጅግ አስፈላጊ መሆኑን በማመንና፣ እንዲሁም ባለው የኑሮ ጠባይ ምክንያት ለመቀራረብ ባለመቻሉ፣ ግንኙነትን ለመፍጠር ነው። 

 

የተመሠረተው ማኅበር በ“IRS Code 501 (C) (3)” የትርፍ አልባ ድርጅት ሕግ ተመርኩዞ ነው። የሞት አደጋ ወይንም ሕመም ሲያጋጥም ለመረዳዳትና ለመፅናናት የተቋቋመ በመሆኑም፣ በሐገር ውስጥ ገቢ የአስተዳደር ደንብ መሠረት ድርጅቶችና ግለሰቦች ለማሕበሩ የሚያደርጉት አስተዋፅፆ ከቀረጥ ነፃ ነው። 

 

አንድ የቤተ ክርስቲያን አባል፤ በተጨማሪ የእድሩም አባል መሆን ከወሰነ በመተዳደሪያ ደንብ ውስጥ የተዘረዘሩትን የአባልነት መስፈርቶች በቅድሚያ ማሟላት ይገባዋል። አባልነት ጊዜ የሚጀምረውም ከተመዘገበበት ዕለት ጀምሮ ይሆናል። ሙሉ የአባልነት መብት የሚኖረውም ክፍያውን ሳያቋርጥ በመክፈልና ግዴታዎችን በሟሟላት አንድ አመት ከቆየ በኋላ ብቻ ነው። 

 

ማሕበሩ የሚተዳደረው (ሀ)ከአባላት ወርሃዊ መዋጮ፤ (ለ)ከደንብ ማስከበሪያ ከሚገኝ ገቢና (ሐ) ከሌሎች ልዩ ልዩ የገንዘብ አመንጪ ከሚሰበሰብ የባጀት ገቢ ነው ። 

 

የአባልነት ግዴታ፤

  • ማሕበርተኛ ከዚህ ዓለም በሞት ቢለይ በፀሎተ ፍትሐት ላይ መገኘት፤ 

  • በቀብር ሥነ ስርዓት ላይ መድረስና ቤተሰቡን ማጽናናት፤ እንዲሁም፥ 

  • በሕመምና በሀዘን ሰዓት በመገኘት የተጠናከረ ማሕበራዊ ግንኙነትን መፍጠር ናቸው። 

 

በጥቅምት 2015 (2008 E.C) በሶስት አድራሻዎች በቨርጂንያ እና በሜሪላንድ አካባቢ የመቃብር ቦታዎች (Plots) እንዲገዙ ተወስኗል። የተመረጡት የመቃብር ክልል ቦታዎች፣ ለደብረ ገነት መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያንም ሆነ ለአባላት የመኖርያ ሰፈር የሚቀርቡ አማካኝ ቦታዎች ላይ ነው። እነዚህም፤ 

 

  • Fairfax Memorial Park Cemetery in Virginia 

  • Resurrection Cemetery in Maryland (Catholic Cemetery) 

  • Gate of Heaven Cemetery in Maryland (Catholic Cemetery)

Contact Us

Thanks for submitting!

Physical Address:

C/O Debre Genet MedhaneAlem Ethiopian Orthodox Tewahedo Church,

4401 Old Branch Avenue, Temple Hills, MD, 20748, USA

Alternate Address:

Debre Genet MedhaneAlem Mutual Aid Association

P.O. Box 1536, Temple Hills, MD, 20757, USA

bottom of page